መልካም ልምድ ከባቲዎች እንውሰድ!
ለመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፋዊ ፈተና ለመውሰድ ወደግቢያችን ከመጡ ተማሪዎች ውስጥ የባቲ ከተማ እና የባቲ ወረዳ ተማሪዎች ይገኙበታል። እነዚህ ተማሪዎች ደንቦችን በማክበርና የፈተና ስርዓትን በሚገባው መልኩ በማክበር አርዓያዎች ነበሩ።
ከዚህ ወጭ የነዚህ ተማሪዎች አስደናቂው ተግባራቸው የዶርም ንጽህና አጠባበቃቸውና ለንብረቶች የነበራቸው ጥንቃቄ ነበር።
ባቲዎች ፈተናቸውን አጠናቅቀው ወደየቤታች ከመሄዳቸው በፊት የሰነበቱባቸውን ዶርሞች አጥበው አስረክበዋል። እናመሰግናለን። ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ ከነዚህ ተማሪዎች ልምድ እንዲወስድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
/ወሎ ዩኒቨርስቲ/
