የአካል ጉዳት ያልበገራት ተማሪ #አጃኢባ_ያሲን ሽኩር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በእግሯ በመሥራት አርአያ ሆናለች።
ተነሳሽነት ካለ አካል ጉዳተኝነት አላማን ከማሳካት እንደማያግድ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በእግሯ እየሰራች ያለችው ተማሪ አጃኢባ ጥሩ ማሳያም ጭምር ሆናለች።
የአካል ጉዳተኝነት ትምህርትን ጨምሮ ከማንኛውም ማኅበራዊ መስተጋብር እንደማያግድ ተማሪ አጃኢባን ማየት በቂ ነው።
ተማሪ አጀኢባ አካል ጉዳተኝነት ግብን ለማሳካት ከመጣር እንደማያግድ ለበርካቶች ማስተማሪያም ጭምር መሆኗን ኢዜአ ዘግቧል።
የተማሪዋ ፈተናውን በእግሯ መሥራት አካል ጉዳተኝነት ተሰጥኦንና ተነሳሽነትን ከግብ ከማድረስ እንደማያግድም አመላካች ነው።
የ/ኢዜአ/ ዘገባ ነው