ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና አቶ አብርሀም ማርሻሎ የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባን አቋርጠው ነው ሐዋሳ የገቡት።
ሁለቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ሐዋሳ የገቡት በዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ላይ የደረሰውን አደጋ እንደሰሙ መሆኑን ታውቋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ እና የብልፅግና ፓርቲ ሀላፊው በተፈጠረው አደጋ የተጎዱ ተማሪዎችን ለማየት ሆስፒታል ቦታው ድረስ በመሄድ መመልከት እና ማፅናናት ችለዋል።
/ሐዋሳ ከተማ ሕዝብ ግንኙነት/