ሰውነት ከመፈጠር እንጅ ከመወለድ አይጀምርም

እውነተኛ ፖለቲከኞች ህዝብን በአንድ ላይ ያሰባስባሉ እንጂ በሰው ሠራሽ ማንነት በመከፋፈል መለያየትን አይፈጥሩም!!

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በአንድ ወቅት እንደተናገሩት “ሁላችንም ዘር አለን ዘሩ ግን እኛ አይደለንም እኛ ሰዎች ነን ሰውነት ከመፈጠር እንጂ ከመወለድ አይጀምርም እና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን” ብለው ነበር።

በአለም አቀፍ ደረጃ ብንመለከት ውጤታማ ፖለቲከኞች ከፓርቲያዊ ጥቅም ይልቅ የማህበረሰቡን ፍላጎት በማስቀደም የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት እና የሚወደዱበት ሁኔታ ለመፍጠር ይጥራሉ ይህ አካሄድ ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ አጠቃላይ የአስተዳደርን ውጤታማነት ያሳድጋል።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የመሰሉ ብሩህ አመለካከት ያላቸው እና በህዝባችን መካከል የጋራ መግባባንት እና በሠላም አብሮ መኖርን የሚያጎለብት መልካም ሃሳብ ያላቸውን ምሁሮችን ያብዛልን!!
/SMART ETHIOPIANS- twiter/

Published by 𝗬𝗮𝘀𝗶𝗻 𝗘𝗻𝗱𝗿𝗶𝘀

Bloger

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started