በህንድ አገር ዝንጀሮዎች የስድስት ዓመት ልጃገረድን ከፆታዊ ጥቃት አዳኑ!
በህንድ አገር ከቤት ውጭ ስትጫወት የነበረች የስድስት አመት ልጃገረድ በአንድ ወጣት አግቶ ኡታር ፕራዴሽ ተብሎ በሚጠራ ሰሜናዊ ግዛት ባግፓት በሚባል ቦታ ከወሰዳት በኋላ ወና ቤት ውስጥ ማስገባቱን ብዙ የህንድ ሚዲያዎች ዘግበዋል ሲል የፃፈው ዴይሊ ሜይል ነው።
የልጃገረዷ ወላጆች ግለሰቡ የተጎጅዋን ወጣት ልብስ አውልቆ ሊደፍራት ቢሞክርም ብዙ ዝንጀሮዎች ገብተው ጥቃት በመክፈት እንዲሰደድ አድርገውታል ሲሉ ተናግረዋል።
ወላጆቿ ይህን ያሉት ከመደፈር የዳነችውና በሁኔታው የተደናገጠችው ልጅ ወደ ቤቷ ተመልሳ ዝንጀሮዎቹ ከሰውየው ‘እንዳዳኗት’ ለወላጆቿ በመናገሯ መሆኑን የሕንድ ታይምስ ዘግቧል።
አባቷ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ሲናገሩ ‘ዝንጀሮዎቹ ጣልቃ ባይገቡ ኖሮ ልጄ አሁን ሞታ ነበር’ ብሏል።
ወጣቱ ግለሰብ የሌላ መንደር ነዋሪ ሲሆን እስካሁን ማንነቱን ማወቅ እንዳልተቻለ ፖሊስ አስታውቋል።
የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ተፈፅሟል በመባሉ የፖሊስ ምርመራ የተከፈተ ቢሆንም ግለሰቡ ከአካባቢው ሸሽቶ የተደበቀ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግሯል ሲል የዘገበው ደይሊ ሜይል ነው።
