አህያ ሁን አለኝ – አህያ ሆንኩለት፣
አሰሱን ገሰሱን – እንድሸከምለት።
መጓዣ ሁን ብሎ – ፈረስ አደረገኝ፣
በየዳገቱ ላይ – ወስዶ ሚጋልበኝ።
እንጃ ከሰሞኑ – በግ ነህ ተብያለሁ፣
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ – አሁን ፈርቻለሁ።

/ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን/

Published by 𝗬𝗮𝘀𝗶𝗻 𝗘𝗻𝗱𝗿𝗶𝘀

Bloger

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started